በቃ ማለት በቃ ነው፤ ካሁን በኋላ በፍፁም አይደገምም!

  مَا لَكُمْ لاَ تُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالْمُسْتَضْعَفِينَ مِنْ الرِّجَالِ وَالنِّسَاءِ وَالْوِلْدَانِ الَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْ هَذِهِ الْقَرْيَةِ الظَّالِمِ أَهْلُهَا وَاجْعَل لَنَا مِنْ لَدُنْكَ وَلِيًّا وَاجْعَل لَنَا مِنْ  لَدُنْكَ نَصِيرًا (النساء:٧٥)

በአላህ መንገድና ከወንዶች፣ ከሴቶችና ከልጆችም የኾኑትን ደካሞች እነዚያን፦ “ጌታችን ሆይ! ከዚች ባለቤቶችዋ በዳይ ከኾኑት ከተማ አውጣን ከአንተም ዘንድ ለኛ አሳዳሪ አድርግልን ከአንተ ዘንድምለኛ ረዳትን አድርግልን።” የሚሉትን (ለማዳን) የማትጋደሉት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ሱረቱ አል-ኒሳእ:75)

በቃ ማለት በቃ ነው፤ ካሁን በኋላ በፍፁም አይደገምም!

እኛ በቴክሳስ ዳላስ ፎርት ዎርዝ አካባቢ የምንኖር ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የእስልምናና ክርስትና ሃይማኖት ተቛማት ላይ በተለይም በተደጋገመና በገዘፈ መልኩ በሙስሊሞች ህይወት፣ ንብረትና መስጊዶች ላይ እየተፈጸሙ ያሉትን ተደጋጋሚ የጥፋት ድርጊቶች እጅግ በመረረ መልኩ እናወግዛለን።

በተለይም በሰሞኑ በአማራ ክልል በሞጣ ከተማ ውስጥ በአንድ ቀን አራት መስጊዶችን ማቃጠል ሳይበቃቸው በሚቃጠሉት መስጊዶች ዙሪያ በመጨፈርና በማቅራራት እንኩዋን ፈጣሪን አውቃለሁ ከሚሉ ሰው መሰሎች ይቅርና ፈጣሪን ከካዱ ሰዎች የማይጠበቅ እንስሳዊ ድርጊት የፈጸሙ ሰዎችን እንዲሁም ካሁን በፊት የተፈፀሙ ተመሳሳይ ግፎችን በቸልተኝነት በመመልከት ለዚህ አሳፋሪ ድርጊት ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቹትን የአማራ ክልል አስተዳደርና የፀጥታ ኣካላት በከፍተኛ ቁጣ እናወግዛቸዋለን።  በአላህ(ሱወ) ፍቃድም ካሁን በፊት እንደነበሩት በደለኞች በተቻለው መልኩ ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጥራለን።

በመረጃ የተደገፈ ታሪክ በግልፅ እንደሚያሳየው ሙስሊም አትዮጵያውያን ካሁን በፊት በነበሩ መንግስታትና መሪዎች የተለያዩ ገፅታ ያላቸው ግልፅና ድብቅ ግፍና በደል ይደርስባቸው እንደነበር ይታወቃል። ከነዚህም ውስጥ ሙስሊሞችን በጅምላ መግደል፣ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ማስገደድ፣ በተወለዱባት ሃገራቸው ውስጥ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመፈረጅ ሃይማኖታቸውን ፈጣሪ ባዘዘው መልኩ እንዳይተገብሩ በማድረግ፣ የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ታሪክ በመካድ፣ በማጠልሸትና በመከለስ ለምዕተ ዘመናት የዘለቁ ግፎችን ማስታወስ የግድ ይላል። አሁን ባለንበት ዘመን እንኩዋን በተለያዩ የሃገሪቱዋ ክፍሎች በተለይም በአክሱም አካባቢ ሙስሊሞችን በትውልድ ስፍራቸው ላይ ፈጣሪን የሚያመልኩበት መስጊድ መስሪያ ቦታ ከመከልከል አልፎ ሲሞቱ እንኩዋን የሚቀበሩበት የመቃብር ቦታ በመከልከል እየደረሰባቸው ያለው ግፍና በደል ከማንም የተደበቀ አይደለም።

አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ከተወለዱበት መሬት ማፈናቀልና የለፉበትን ንብረታቸውን መዝረፍ ሳያንሳቸው በሞጣ ከተማ እንደታየው የአለማት ጌታ አላህ (ሱወ) ማምለኪያ ቤት የሆኑ አራት መስጊዶችን በማናለብኝነት ስሜት በእሳት እያነደዱ ዙሪያውን ከበው በመጨፈርና በመፎከር ስብዕና ፈጽሞ የጠፋበት ድርጊታቸው በማንኛውም ቦታ ያለን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “በቃ ማለት በቃነው ካሁን በኋላ በፍፁም አይደገምም!” ብለን በቁርጠኝነት እንድንነሳ አስገድዶናል።

በዚህም የተነሳ እኛ በቴክሳስ ዳላስ ፎርት ዎርዝ አካባቢ የምንኖር ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን፦

፩) በሞጣና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈፀሙ የማፍረስና የማቃጠል ድርጊቶችን በከፍተኛ ድምፅ እናወግዛለን፤

፪) የፌደራልና የክልል መንግስት አካላት እነዚህን እኩይ ተግባራትን የፈፀሙትን፣ ከጀርባ በመሆንም እንደዚህ አስፀያፊ ድርጊቶችን ያቀነባበሩትን መሰሪ ወንጀለኞችን በፍጥነት ለፍርድ እንዲያቀርቡ አበክረን እንጠይቃለን፤

፫) የፌደራልና የክልል መንግስት አካላት ለጠቅላላው የሃገሩቱ ህዝብ ያለባቸውን ሃላፊነት ከማንኛውም የዘር የሃይማኖትና የጎሳ አድልዎ በፀዳ መልኩ እንዲወጡ ይህንንም ከወገንተኝነት ነፃ የሆነ አስተዳደራዊ ስራ የሚያውኩ በየደረጃው የተሰገሰጉ ሃላፊዎችና አማካሪዎች ላይ አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወስዱ አበክረን እንጠይቃለን፤

፬) ካሁን በፊት የሱማሌ ክልል መንግስት እንዳደረገው በየቦታዎች ለተፈፀሙ በደሎች የሚመለከታቸው ክልሎች በተለይም 21 መስጊዶች ሲቃጠሉ በቸልተኝነት የተመለከተው የአማራ ክልል መንግስት የጥቃቶቹን ሰለባዎችና ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ይቅርታ እንዲጠይቅ ለተጎዱ ሰዎችም ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንዲሁም የተቃጠሉና የፈረሱ የሃይማኖት ተቛማትን በራሱ ወጪ በተቻለ ፍጥነት መልሶ እንዲያሰራ እንጠይቃለን፤

፭) እንዲህ ኣይነት አሳፋሪ ድርጊቶች ዳግም እንዳይፈፀሙ የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል መንግስትና የፀጥታ አካላት ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና የሃይማኖት ተቛማት እኩልና ዘላቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለሃገራችን ያለን ጥልቅ ውዴታ ምንጩ መሬቱና ተራራው ሳይሆን እስልምና መሆኑን ማንም ሰው ሊያውቀው ይገባል። እኛ ለሃገራችን ስንለፋና ስንሰዋ እስልምና ለሃይማኖታችን፣ ለራሳችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለዘመዶቻችን፣ ለንብረታችንና ለሃገራችን አስፈላጊውን ሁሉ መስዋእትነት እንድንከፍል ስለሚያዘን ነው። አላህ (ሱወ) በቁርአን ውስጥ እንዳዘዘን ስግደታችንም መገዛታችንም መኖራችንም ሆነ መሞታችን ለአለማት ጌታ አላህ (ሱወ) ብቻ መሆኑን ማንኛውም በእስልምና ላይ የተሳሳተ አመለካከት ያለው ሰው ጠንቅቆ ቢያውቅና ሁሌም ቢያስታውስ ይበጀዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እጅግ በጣም ታጋሾችና በፈጣሪያችን ብቻ የምንመካ ብንሆንም በደል ሲበዛብን በተለይ በሃይማኖታችን በመጡ ጉዳዮች ላይ በፍፁም የማንደራደርና ካሁን በፊት የነበሩትን ጨቛኝና በዳይ ሥርዓቶችን የገረሰሱ አንፀባራቂ ትግሎች ጀማሪና ዋነኛ አካል እንደነበርን ሁሌም ማስታወስ ይገባል።

አላህ (ሱወ) ህዝባችንና ሃገራችንን እንዲጠብቅልን እንለምነዋለን። በየትኛውም ስፍራ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን ሃገራችንን ወደ ብጥብጥና እርስ በርስ መተላለቅ እንድንገባ በግልፅና በስውር የሚንቀሳቀሱ መሰሪ አካላትን ሴራ ለማክሸፍ አስፈላጊውን ርብርብና ያላሰለሰ ጥረት እንድናደርግ በፈጣሪያችን ስም ጥሪ እናቀርባለን።

ቢላል ኮሚኒቲ ሴንተር

ዳላስ-ፎርት ዎርዝ, ቴክሳስ

December 24, 2019

 

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ

In the name of Allah the most merciful the most compassionate

  مَا لَكُمْ لاَ تُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالْمُسْتَضْعَفِينَ مِنْ الرِّجَالِ وَالنِّسَاءِ وَالْوِلْدَانِ الَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْ هَذِهِ الْقَرْيَةِ الظَّالِمِ أَهْلُهَا وَاجْعَل لَنَا مِنْ لَدُنْكَ وَلِيًّا وَاجْعَل لَنَا مِنْ  لَدُنْكَ نَصِيرًا – النساء:٧٥

And what is [the matter] with you that you fight not in the cause of Allah and [for] the oppressed among men, women, and children who say, “Our Lord, take us out of this city of oppressive people and appoint for us from Yourself a protector and appoint for us from Yourself a helper?” (al-Nisa:75)

Never Again! Enough is Enough!

We, Muslims of Ethiopian origin residing in the Dallas-Fort Worth metroplex of Texas, vehemently condemn the recent shameful destruction of Muslim and Christian religious establishments, particularly the repeated and severe brutalities against Muslim lives and properties.

Most notably, we are extremely angered by and fervently express our extreme abhorrence at the recent simultaneous burning of four mosques in the city of Mota that was fueled by the continuous indifference and inaction of the Amhara regional state officials and security forces that enabled such shameful and barbaric acts. These cowards not only set four mosques ablaze but also were recorded singing and dancing around the burning mosques proving their complete lack of humanity as well as their irreligious and barbaric state of mind. We will do our utmost to facilitate these cowards are fated to justice in the same manner as other previous oppressors.

It is historically evident that Muslim Ethiopians have endured centuries of clear and tacit oppressions and brutality from previous regimes. Muslims were massacred, excessively brutalized and forced to denounce their religion, summarily categorized as secondary citizens and prevented from properly practicing their religion. In addition, Ethiopian Islamic history has been blatantly altered, blemished and shamelessly rejected for centuries. Even now, it is widely known that Muslims in Ethiopia, especially in Axum area, continue to be subjugated through systematic and blatant denial of their basic human right to establish places of worship and burial sites in their own birthplaces.

The most recent vicious and barbaric acts of setting the four mosques on fire in Mota coupled with the perpetrators utter lack of humanity manifested through their dancing and singings around the burning mosques as well as the ongoing brutalities, displacements and destruction of their hard-earned possessions have exhausted our patience and forced as to stridently declare Enough is Enough and Never Again! As a result, we Muslims of Ethiopian origin residing in the Dallas-Fort Worth metroplex:

  1. vehemently condemn the various destructions of religious establishments and barbarism in Mota and other parts of the country;
  2. urge the federal and regional government officials to expeditiously apprehend and bring to justice both the perpetrators of these barbaric acts as well as their shadowy backers and organizers;
  3. urge the federal and regional government officials to discharge their responsibility of governance and protecting every citizen without any ethnic or religious bias and extricate themselves from officials and advisors at all government levels with proven bias against any religious or ethnic group;
  4. uge the reginal governments (especially the Amhara regional government that enabled the destruction of 21 mosques through its indifference and inaction) to apologize to the victims and Muslim Ethiopians, pay appropriate restitutions and rebuild the affected religious institutions and structures at their own expense in the same manner as the Somali regional government did previously;
  5. urge the federal and regional government officials and security forces to provide equal, adequate and sustained protection for each citizen and religious institution and actively prevent such future occurrences.

Everyone should note that the source of Muslim Ethiopians’ deep love for our country is Islam itself and not the land or terrains. Our tireless efforts and sacrifice for our country originate from our Islamic obligations to our religion, ourselves, our family, our neighbors, our kin, our belongings and our country. Any person with the slightest misapprehension about Islam and Muslims should remember that our prayer, sacrifice, life and death are only to the lord of the universe, Allah (swt). We Muslim Ethiopians are extremely tolerant, and we only bow to and solely depend on our creator. However, it is worthwhile remembering that we never compromise on matters of our religion and have initiated and spearheaded the most distinguished resistances and struggles against previous regimes that resulted in their eventual demise.

We appeal to Allah (swt) to protect our people and country. We, in the name of our creator, also call on Ethiopians everywhere to work together and neutralize the open and tacit plots of various nefarious groups pushing to thrust us towards chaos and mutually assured destruction.

Bilal Community Center

Dallas-Fort Worth, Texas

December 24, 2019

Eid Mubarak

May Allah bring you joy, happiness, peace and prosperity on this blessed occasion. Wishing all our community members, their families and Muslims all over the world on this happy occasion of Eid! Eid Mubarak!

May Allah flood your lives with happiness on this occasion, your heart with iman, your soul with yaqeen, your mind with wisdom. BCC Board of directors invites all muslims of Ethiopian heritage in the DFW area to come together and collectively promote our beautiful Islamic way of life. wishing you all the very best Eid.

BCC Board of Directors.

Press Release: Over Ethio Muslims Arbitration Committee False Allegations

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ

በዳላስ ቴክሳስ የሚገኘው የቢላል ኮሚኒቲ በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ላይ የሚነዙትን ሀሰተኛና መሰረተቢስ ወሬዎች በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን ይህ እኩይ ተግባር እነዚህ ጥቂት ስም አጥፊ ግለሰቦችና ደጋፊዎቻቸው የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ በጉልህ ያሳያል። ቢላል ኮሚኒቲ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው መሪዎች በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ ወቅታዊና ተገቢ መሆኑን ያምንበታል። የቢላል ኮሚኒቲ እነዚህ ግለሰቦች የኮሚቴው መሪዎች በይቅር ባይነት “ተመከሩ፣ ተውባ አድርጉ፣ ኮሚቴውንም ይቅርታ ጠይቁ!” በሚል ያቀረቡትን እስላማዊ የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከእኩይ፣ ከፋፋይና አፍራሽ ተግባራቸው እንዲታቃቡ ይመክራል።

ታሪክን መለስ ብሎ ለሚቃኝ ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያውን ጨቋኝ ሥርዓቶችን  ለመለወጥና በምትኩ የህዝቦችን መብት የሚያከብር ሥርዓት ለመገንባት ለዘመናት ሲታገሉ ኖረዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውንም በዜግነት የሚደርሱ በደሎችና ጭቆናዎችን ከመታገል በተጨማሪ ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን ለማስከበር በዚህ ረጅም የትግል ሂደት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ይታወቃል። ይሁንና ሙስሊሙ ህብረተሰብ በየዘመናቱ ከተከሰቱት ለውጦች የሚገባውን ያህል ተጠቃሚ ሳይሆን መቆየቱ በገሃድ የሚታይ እውነታ ነው። ለዚህ መሰረታዊ ችግር ከሆኑት ውስጥ የሙስሊሙ የትግል ግብ አቅጣጫውን በውል ያልለዬ፣ እንቅስቃሴው የተበታተነና አመራሩ ቅንጅነ የጎደለው መሆኑ የራሱ ድርሻ እንደነበረው ግልጽ ነው።

ረጅሙን ታሪካዊ ሂደት አልፈን ወደአሁኑ የሙስሊም ኢትዮጵያውን የእንቅስቃሴ ስንመለስ የሙስሊሙ ትግሉ እምርታዊ ለውጥ አሳይቷል። የዚህ እምርታዊ ለውጥ አንዱና ዋናው መሰረት በትግሉ ሂደት ነጥሮ የወጣው የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች በሳልና ቆራጥ አመራር መሆኑ ከህዝበ ሙስሊሙ ባሻገር የእንቅስቃሴው ደጋፊ የነበረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው ሀቅ ነው። የአሁኑ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ የጠራ ግብ ያለው፤ በዲስፕሊን የመሪዎቹን መመሪያ የሚከተል ሰላማዊ ማህበረሰብ የፈጠረ፤ የተቀናጀ፣ በሳልና ጠንካራ መሪዎች የሚመሩት፣ ራሱን ችሎ ታግሎ የሚያታግል፣ በአርአያነት የሚጠቀስ ህዝባዊ ትግል ነው። ሂደቱን በገለልተኝነት የሚከታተሉ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጠበብትም የሙስሊሙ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ሰላማዊ የትግል ሂደት ውስጥ ፈር ቀዳጅ ሰላማዊ ትግል መሆኑን መስክረውለታል። በኋላም በመላ ኢትዮጵያ ለተቀጣጠለው ሰላማዊ ትግል መነሻውና መሰረቱ ይህ የሙስሊሙ ጠንካራና ለዓመታት የዘለቀ እልህ አስጨራሽ ትግል ነው። የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ለዚህ የበቃው ደግሞ በግንባር ቀደምነት የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች በሰጡት የሰከነና ቆራጥ አመራር መሆኑ ለአፍታ እንኳ ሊዘነጋ አይችልም።

ይህ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ መሰረቱ አገር ቤት ያለው ህዝበ ሙስሊምና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በውጭ ሀገር የምንኖረውም ለትግሉ ድጋፍ በማድረግ የድርሻችንን እያበረክትን እንገኛለን። አሁንም በውጭ አገር ከምንኖረው የሚጠበቀው ይህን መሰል የትግል አጋርነት እንጂ በሬ ወለደ በሚል አሉባልታ በትግል ተፈትነው ብቃታቸውን ያስመሰከሩትን በሳልና ባለራዕይ የኮሚቴ መሪዎች ወደኋላ መጎተትና ስማቸውን በሀሰት ማጠልሸት ብሎም ህዝበ ሙስሊሙን መከፋፈል ሊሆን ፈጽሞ አይገባም።

አሁንም በድጋሚ የቢላል ኮሚኒቲ በዚህ አፍራሽ፣ ከፋፋይና እኩይ ተግባር የተሰማሩ ወገኖች ተመከሩ፣ ድጋፍ መስጠት ባትችሉ እንቅፋትና ጎታች ከመሆን ታቀቡ እንላለን። ይህን የሰላም ጥሪ ጥሰው በእኩይ ዘመቻቸው ለሚቀጥሉ ወገኖች ግን የቢላል ኮሚኒቲ በተናጠልም ሆነ ከሌሎች እህት ኮሚኒቲዎች በጋራ በመሆን አስፈላጊና ተገቢ የሆነ ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ የማይል መሆኑን ያስገነዝባል።

በዚህ አጋጣሚ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ እህት ኮሚኒቲዎች እነዚህ በኮሚቴው መሪዎች ላይ አሉባልታና መርዝ የሚነዙ ግለሰቦች በመከከላችን የሚኖሩ እንደመሆኑ ተመክረው ካልተመለሱ አፋጣኝና የማያዳግም የተቀናጀ እርምጃ እንድንወስድ ጥሪ ያቀርባል።

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን!

የቢላል ኮሚኒቲ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ዳላስ፣ ቴክሳስ

ጁን 3፣ 2018 G.C.